የሚፈልጉበት ቦታ ያደርስዎታል ...

ይህ በአገርዎ፣ በኩንባያዎ፣ ወይም ካምፓስ ውስጥ ታግዷል?

አለማችን ላይ ያሉ አፋኝ መንግስታት አሰራርን ስለምናውቅ የሚፈልጉትን ይዘት በሚፈልጉት ቦታ እና ወቅት እንዲያገኙ በተለየ ሁኔታ ለመርዳት ልምዱ አለን።

...እናም ያለ ችግር ያደርስዎታል።

ለህዝብ ክፍት የሆነ WiFiን ሲጠቀሙ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ መዳሰስ ይፈልጋሉ?

ነጻ የኢንተርኔት አገልግሎት አሪፍ ነው ነገር ግን የተሰረቁ ኩኪዎች እና መለያዎች ግን አይደሉም። Psiphon ለመገናኘት የሚጠቀሙት ኔትወርክ ምንም አይነት ቢሆን ጤነኛ የኢንተርኔት መንገድ ይሰጦታል።

እምነት፣ ፍጥነት፣ ቀላልነት፡- ሦስቱንም ያግኙ

ኤ.ኤ.አ. ከ2008 ጀመሮ Psiphon በአለም ላይ ነጻነታቸው ውስን በሆነባቸው ሃገራት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የታገደ እውቀትን እና ሃሳቦችን እንዲያገኙ ረድቷል። አሁን Psiphon ይህንን ለእርስዎ ማድረግ ይችላል።

Psiphon ምንድን ነው?

Psiphon ያልተገደበ የኢንተርኔት ይዘትን እንዲያገኙ የሚያስችል የVPN, የSSH እና የHTTP ወኪል ቴክኖሎጂን የሚጠቀም በPsiphon ኩባንያ የተሰራ የማለፊያ መሳሪያ ነው። የPsiphon ደምበኛዎት እገዳውን ለማለፍ የሚያስችል እድልዎን ለማስፋት አዳዲስ የመገናኛ ቦታዎን በራስሰር ያውቃል ።

Psiphon የተሰራው የመስመር ላይ ክፍተ ምንጭ ይዘቶችን ለማቅረብ ነው። Psiphon የመስመር ላይ ግላዊነትዎን ስለማይጨምር እንደ የመስመር ላይ የደህንነት መሳሪያ መታየት ወይም ጥቅም ላይ መዋል የለበትም።